Fana: At a Speed of Life!

 ለአፍሪካ ዋንጫ የተለያዩ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች አቢጃን እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የተለያዩ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች ወደ አቢጃን እየገቡ ይገኛሉ፡፡

ትናንት ምሽት የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን  የሴኔጋል  ብሄራዊ ቡድን ኮትዲቯር የገባ ሲሆን÷ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ከልዑካን ቡድኑ ጋር አቢጃን ገብተዋል፡፡

የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫየፍፃሜ ተፋላሚው የግብፅ ብሄራዊ ቡድንም በተመሳሳይ ከደቂቃዎች በፊት ኮትዲቯር ደርሷል፡፡

የሊቨርፑሉን ኮከብ ሞሀመድ ሳላህ ያካተቱት ፈርዖኖቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመጪው እሁድ ከሞዛምቢክ ጋር ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የደቡብ አፍሪካ እና ታንዛኒያ ብሄራዊ ቡድኖችም በትናንትናው እለት ወደ አዘጋጇ ሀገር የገቡ ሲሆን÷ የጊኒ ቢሳው ብሄራዊ ቡድን ቀደም ሲል ወደ ኮትዲቯር ያቀና የመጀመሪያው ብሄራዊ ቡድን መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ቅዳሜ አዘጋጇ ኮትዲቯር ከጊኒ ቢሳው ጋር ቀን 11 ሰዓት ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.