Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ4 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ4 ሺህ ቶን በላይ የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አማኑኤል ብሩ÷ ያረጁና ምርት የማይሰጡ የቡና ተክሎችን በማደስ የቡናን ምርታማነት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ከ9 ሺህ 900 በላይ ሄክታር መሬት የቡና እድሳት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው÷ ምርት መቀነስ የጀመሩ ተክሎችን በጉንደላ የማደስ ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

የቡናን ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል የጠቆሙት ም/ዋና ዳይሬክተሩ÷ ሥራው በክልሉ ቡና አብቃይ አካባቢዎች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ለጉንደላና ንቅለ ተከላ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከ34 ሚሊየን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች የማፍላትና የእንክብካቤ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተግባሩ ሒደት አርሶ አደሩን ባለቤትና ቀዳሚ ተሰላፊ ለማድረግ የምክክርና የንቅናቄ መድረኮችን በማከናወን የጋራ መግባባት እንደተፈጠረ መናገራቸውንም የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.