Fana: At a Speed of Life!

የ2023 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ኮትዲቯር

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮትዲቯር ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው።

የውድድሩ ተሳታፊ ሀገሮች ኮትዲቯር ገብተው የውድድሩን መጀመር በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

የዘንድሮሮውን አህጉራዊ ውድድር ያዘጋጀችው ኮትዲቯር በፈረንጆቹ መስከረም 2002 የተከሰተው ወታደራዊ አመፅ ብዙ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራዎችን አስከትሎባት ነበር።

ይህ ቀውስ ለዓመታት ቀጥሎ በፈረንጆቹ 2007 መጋቢት 4 ላይ በተከናወነ የሰላም ስምምነት እንዲቋጭ ተደረገ።

በወቅቱ ግጭት ውስጥ የገቡ ሃይሎች ወደ ሰላም ስምምነት እንዲመጡ በማድረግ በኩል በተለይ በሀገሪቷ እግር ኳስ ታሪክ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው ዲዲየር ድሮግባ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ተጫዋቹ በቡዋኬ ከተማ በተካሄደ የብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ ማዳጋስካር ላይ ጎል አስቆጥሮ ሀገሪቱን ለአፍሪካ ዋንጫ ካሳለፈ በኋላ ተዋጊ ሀይሎቸ ተኩስ እንዲያቆሙ ተንበርክኮ መለመኑ ለሁለቱ ወገኖች ወደ ስምምነት ምክንያት መሆኑ በስፋት ይነገራል፡፡

በዚህ ሁኔታ የመጣው የሀገሪቱ ሰላም ከሶስት አመታት በኋላ መልሶ የመደፍረስ አደጋ አጋጠመው።

በፈረንጀቹ 2010 በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የወቅቱ የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት የነበሩት ሎረን ባግቦ ሽንፈታቸውን አምነው መቀበል በመቸገራቸው የተነሳ ሀገሪቱ መልሳ ቀውስ ውስጥ ገባች።

ይህ ሁኔታ በቀጣናው ሀገሮችና በሌሎች አካላት አማካኝነት እንዲረግብ ተደርጎ በምርጫ ያሸነፉት አላሳን ዋታራ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ተደርጎ ቀውሱ የተፈታበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ይህንን እና ሌሎች ግጭት ቀስቃሽ ሁኔታዎች በዓለም ቀዳሚ የካካዋ አምራች ከሆኑ ሀገሮች መካከል አንዷ የሆነችውን ኮትዲቯርን በእጅጉ ፈትነዋታል።

በተደጋጋሚ የተፈተነችው እና ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታ የነበረችው ኮትዲቯር ከፈርንጆቹ 2011 ወዲህ ከነበረችበት የቀውስ አዙሪት ውስጥ መውጣት በመቻሏ ፊቷን ወደ ልማት ለማዞር አስችሏታል።

በርካታ ከዋክብት እግር ኳስ ተጫዋቾችን ያፈራቸው ኮትዲቯር የ2023ቱን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ በካፍ ተመርጣ ለአመታት ዝግጀት ስታደርግ ቆታለች፡፡

ቢቢሲ ስፖርት እንዳስነበበውም ሀገሪቱ በነገው እለት የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ አራት ስታዲየሞችን የገነባች ሲሆን ሁለት ስታዲየሞችን ደግሞ እያስጠገነች ትገኛለች፡፡

በተጨማሪም አቢጃን፣ ቡዋኬ፣ ኮርሆጎ፣ ሳን ፔድሮ እና ሙሳኮሮ በተባሉ ከተሞች የሚገኙ የአየር ማረፊያዎችን፣ መንገዶችንና ሆቴሎችን እድሳት ማከናወኗ ተገልጿል፡፡

አሁንም በድህነት ውስጥ የምትገኘው ኮትዲቯር ያሰናዳችው የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ትልቅ የኢኮኖሚ መነቃቃት ይፈጥርላታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.