Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈች።

የኬፕ ቨርዴን የማሸነፊያ ግቦች ሞንቴሮ እና ሮድሪጌዝ ሲያስቆጥሩ፥የጋናን ብቸኛ ግብ ደግሞ ጂኩ አስቆጥሯል።

በተመሳሳይ በምሽት 2 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ግብፅ እና ሞዛምቢክ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ፈርኦኖች በ2ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠሯት ግብ መሪ መሆን ችለው ነበር።

ይሁን እንጂ ሞዛምቢኮች ከእረፍት መልስ ባስቆጠሯቸው 2 ግቦች እስከመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ድረስ መሪ መሆን ችለዋል፡፡

በመጨረሻም ፈርኦኖቹ በተጨማሪ ሰዓት ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት በማስቆጠር ጨዋታው 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.