Fana: At a Speed of Life!

ሴኔጋል ጊኒን 2 ለ 0 ካሜሮን ደግሞ ጋምቢያን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈች

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በተደረጉ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 3 ጨዋታዎች ሴኔጋል ጊኒን 2 ለ 0 ካሜሮን ደግሞ ጋምቢያን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ሴኔጋል በ61ኛው እና በ90ኛው ደቂቃዎች በተቆጠሩ ግቦች አሸናፊ ሆናለች፡፡

ካሜሮንም በ56ኛው፣ 87ኛው እና በ91ኛው ደቂቃዎች በተገኙ ግቦች አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡

የካሜሮንን ሁለተኛ ጎል የጋምቢያው ተጫዋች በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡

የምድብ 4 ጨዋታዎች ከምሽቱ 5 ሰዓት ሲካሄዱ ሞሪታኒያ ከአልጄሪያ እንዲሁም አንጎላ ከቡርኪናፋሶ የሚገናኙ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.