Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ማክሰኞ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ጥር 21ቀን እንደሚጀመር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

መርሐ ግብሩ ከጥር 21 እስከ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለተከታታይ 6 ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡

ውድድሩ  ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና ተቋማት የውድድር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ውድድሩ በካሜሮን ለሚካሄደው 23ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ በጋና አክራ ለሚካሄደው የመላው አፍሪካ ውድድር እና በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶ አቋማቸውን እንዲፈትሹ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በውድድሩ ከአንድ  እስከ ሦስት የሚወጡ እና ሚኒማ የሚያሟሉ አትሌቶች በቀጣይ በአህጉራዊ  ውድድሮች ኢትዮጵያን እንደሚወክሉ ተጠቁሟል።

ከ40 በላይ የውድድር ተግባራት በሚካሄዱበት በዚህ ውድድር÷ ከ5 ክልሎች፣ ከከተማ አስተዳደሮች ፣ ከ27 ክለቦች እና ተቋማት የተወጣጡ 1 ሺህ 102 አትሌቶች እንደሚሳፈቱ ተጠቅሷል፡፡

ለውድድሩም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መያዙኑ ነው የተገለጸው፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.