Fana: At a Speed of Life!

አማራ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ወደ ክልሉ ከመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም አስታወቀ፡፡

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ እምቢያለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ከ 4 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ወደ ክልሉ መጥተዋል፡፡

በተጨማሪም 10 ሺህ 500 የውጭ ጎብኝዎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.