Fana: At a Speed of Life!

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን እና ሻሸመኔ ከተማ ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ግብ ወገኔ ገዛኸኝ ሲያስቆጥር÷ የሻሸመኔ ከተማን ደግሞ አብዱልቃድር ናስር አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል እና ፋሲል ከነማን ያገናኘው ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.