Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የወንጪ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበት ታላቁ የወንጪ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተካሄደ፡፡

በውድድሩ በሴቶች ጌጤ አለማየሁ፣ ፎትን ተስፋዬ እና ኑሪት አህመድ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በቀዳሚነት አጠናቀዋል።

በወንዶች ደግሞ አትሌት አዲሱ ነጋሽ፣ ሞገስ ንኡማንና ኤሊያስ ጫኔ ተከታትለው በመግባት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ውድድሩን በቀዳሚነት ላጠናቀቁ አትሌቶች 150 ሺህ፣ ሁለተኛ ለወጡት 90 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለወጡት ደግሞ 80 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል።

ሀገራዊ ከሆኑ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም በተዘጋጀው በዚህ ሩጫ ታዋቂ አትሌቶች፣ አንጋፋ አትሌቶች እንዲሁም ታዳጊ አትሌቶች ተሳትፈዋል።

በውድድሩ 2 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከ22 ክለቦችና የማሰልጠኛ ተቋማት የተወጣጡ 302 አትሌቶች ተሳትፈዋል።

ከኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ባሻገርም የኬንያ እና ኡጋንዳ አትሌቶችም ተካፍለዋል።14:06

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.