Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በአስታና የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በካዛኪስታን አስታና በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡

አትሌቱ 7 ደቂቃ ከ33 ሴኮንድ ከ85 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ነው የዓመቱን የ3 ሺህ ሜትር ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ማሸነፉን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላከተው፡፡

የ3 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን 7 ደቂቃ ከ26 ሴኮንድ ሲሆን በኬኒያዊው አትሌት ዳንኤል ኮሜን የተያዘ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.