Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳይጠበቅ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኤፍሬም አሻሞ፣ ቻርለስ ሙሲጌ እና ሱራፌል ጌታቸው የድሬዳዋን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ድሬዳዋ ነጥቡን 14 በማድረስ ለጊዜው 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፈረሰኞቹ በበኩላቸው በ21 ነጥብ በነበሩበት 3ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገደዋል፡፡

የ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከሃምበሪቾ ዱራሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ሀምበሪቾ ዱራሜ በበረከት ወንድሙ ሁለት ጎሎች ሲዳማ ቡና 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በውጤቱ መሰረትም ሀምበሪቾ ዱራሜ ነጥቡን ወደ 6 ከፍ በማድረግ በነበረበት 16ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በተመሳሳይ ሲዳማ ቡና በ15 ነጥቦች በነበረበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.