Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ 57 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 57 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ሃላፊ መስከረም ደበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ ግብር ከፋዮችና መዘጋጃ ቤት አገልግሎት 144 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

እቅዱን ለማሳካትም ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ባለፉት ስድስት ወራትም 70 ነጥብ 71 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 57 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል፡፡

በዚህም የእቅዱን 81 በመቶ ማሳካት መቻሉን ጠቁመው÷ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

በክልሉ 517 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች መኖራቸውን የገለጹት ሃላፊዋ÷ ከዚህም ውስጥ 87 በመቶ የሚሆኑት የ”ሐ” ግብር ከፋዮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያቀርቡና ያለ ደረሰኝ አገልግሎት እና እቃ የሚሸጡ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠርም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.