Fana: At a Speed of Life!

2ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ከ16ኛ ሳምንት ጀምሮ የሚካሄዱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ 2ኛ ዙር ጨዋታዎች ደግሞ ከየካቲት 21ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡

የውድድሩ መርሐ ግብርም በቀጣይ ቀናት የሚገለጽ መሆኑን  የአክሲዮን ማህበሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታድየም  የሜዳና ቴክኒካል ክፍሎች ባለፈው ሳምንት በፊፋ ባለሞያዎች ምዘና የተደረገበት ሲሆን የአውቅና ውጤቱ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.