Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል አቀፍ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የመላ ጋምቤላ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በጋምቤላ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

ውድድሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት÷ ስፖርት የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ ስላለው ውድድሩን በጨዋነት ማካሄድ ይገባል።

በመሆኑም ውድድሩ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ፍፃሜውን እንዲያገኝ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ውድድሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ለመምርጥና ለማብቃት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ለስፖርቱ መጠናከር የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ጠቁመው÷ ውድድሩ በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኒያል ቱት በበኩላቸው÷ ኮሚሽኑ ክልሉን የሚወክሉ ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ የተጀመረው አስረኛው የመላ ጋምቤላ ዓመታዊ የወረዳዎች ስፖርት ውድድር የጥረቱ አካል እንደሆነ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በውድድሩ ጋምቤላ ከተማ አስተዳድርን ጨምሮ 14 ወረዳዎች በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በአትሌቲክስና በሌሎች የስፖርት ዓይነቶች እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.