Fana: At a Speed of Life!

የሸገር ከተማ አሥተዳደር ለ27 ትምህርት ቤቶች ኮምፒተሮችን አሰራጨ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸገር ከተማ አሥተዳደር ለ27 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 125 ኮምፒተሮች ማሰራጨቱን አስታወቀ፡፡

ድጋፉ የግብዓት እጥረትን ለማቃለል እና የዲጂታል ቤተ-መጽሐፍትን ለማጎልበት ያለመ መሆኑን የሸገር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ፊራኪያ ካሣሁን ተናግረዋል፡፡

አሥተዳደሩ 11 ሚሊየን ብር የሚጠጋ በጀት መድቦ ኮምፒዩተሮችን ከተሟላ ግብዓት ጋር ገዝቶ ለትምህርት ቤቶቹ ማሰራጨቱንም ጠቅሰዋል፡፡

የግብዓት ዕጥረት ያለባቸው ትምህርት ቤቶችን የመደገፉ ሥራ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.