Fana: At a Speed of Life!

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለሲዳማ ክልል የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ተቋማትን ለማጠናከር የሚያገለግሉ የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፍ የተደረጉት የደህንነት ካሜራዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ አቅምን የተላበሱ ናቸውም ተብሏል፡፡

25 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ካሜራዎች የሐዋሳ ከተማን ብሎም የክልሉን ፖሊስ አሰራር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማዘመን የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው በርክክቡ ወቅት ተገልጿል፡፡

ድጋፉ ኢንስቲትዩቱ ከክልሉ መንግሥት ጋር ካለው የቀደመ መልካም ግንኙነት ጋር ተያይዞ ክልሉን በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለመደገፍ የገባውን ቃል ያረጋገጠበት ነው፡፡

ካሜራዎቹን እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ እና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለሞያዎች በሲዳማ ክልል በመገኘት ንብረቶቹን አስረክበዋል፡፡

ንብረቶቹን የተረከቡት የክልሉ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አለማየሁ ጢሞቲዎስ÷አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለክልሉ ስላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ድጋፍ የተደረጉት ቴክኖሎጂዎች ክልሉን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ላይ የሚኖራቸው ሚናም ከፍተኛ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.