Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በኢነርጂና አቪዬሽን ዲፕሎማሲ መስክ ትብብር እንዲኖር  በትኩረት እየሰራች  መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በኢነርጂና አቪዬሽን ዲፕሎማሲ ቀጣናዊ ትስስር ለመፍጠር ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር)በወቅታዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ በቀጣናው በኢነርጂና አቪዬሽን ዲፕሎማሲ መስክ ትብብር እንዲኖር እየሰራች መሆኑን ተናግዋል፡፡

በዘርፎቹ መሰል ሥራ ለማከናወንም ኢትዮጵያ ሰፊ አቅም አላት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ ወንዞች ባለቤት ናት ያሉት አምባሳደሩ÷የንፋስ ሃይል እና የጸሃይ ሃይል ማመንጨት የሚያስችል አቅም መኖሩንም አንስተዋል፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ጎረቤት ሀገራት ያላቸውን የሃይል አቅርቦት ችግር እንደሚቀርፍም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከኬንያ ጋር የ25 ዓመት የኤሌክትሪክ ግዥ ስምምነት መፈረሙን በመግለጽ ከሌሎች ሀገራት ጋርም በጋራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ወደፊት የኤሌክትሪክ ሽያጭ እስከ ስፔን እንደሚደርስ ጠቁመው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያና በታንዛኒያ የነበራቸው ጉብኝት የኢነርጂና የአቪዬሽን ትብብርን ለማጠናከር ያለመ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ለታንዛኒያ 400 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ሽያጭ ለማቅረብ ከስምምነት መደረሱን የገለጹት አምባሳደር መለስ÷ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር መስራት የሚፈልጉ ሀገራት እንዳሉም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁለንተናዊ አቅሙ እያደገ መምጣቱንም ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.