Fana: At a Speed of Life!

ታላቁን የረመዳን ወር በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል – ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁን የረመዳን ወር በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ገለጹ።
 
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የረመዳን ወርን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በመግለጫቸውም፤ የምንቀበለው የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የዒባዳ ወር ይሁንልን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
 
ታላቁ የረመዳን ወር የእዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የምህረት ወር መሆኑን አንስተዋል።
 
በመሆኑም ደካሞችን፣ ችግረኞችን፣ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመርዳትና ማዕዳችንን በማካፈል በመተሳሰብና አላህን በመለመን ወሩን ማሳለፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
 
ፕሬዚዳንቱ ለመላው ሙስሊም ማኀበረሰብ ‘እንኳን ለ1445 ዓ.ሂ የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ” በማለት የመልካም ምኞት መልዕክት ማስተላለፋቸውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ መረጃ አመልክቷል።
 
መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው ሰላም ሲኖር መሆኑን ገልጸው፤ ለሀገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን ደኅንነት ዱዐ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.