Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የ16 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ16 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት አፅድቋል፡፡

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን÷ በስብሰባውም በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስርዓትን ለማሻሻል እና ለማዘመን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትን መርምሮ አጽድቋል፡፡

የምክር ቤት አባላትም የዳኞችን ሹመት አስመልክቶ በሰጡት ሃሳብ የዳኝነት ስርዓቱ ሀገርን መምሰል እንዳለበት በመግለጽ ዳኝነት ነጻነት እንዲኖረው አሳስበዋል፡፡

ዳኞች ለሹመት ሲመለመሉ ፈተናዎችን እንደወሰዱ የተገለጸ ሲሆን÷ አመራረጡም ኢትዮጵያን እንዲመስል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ሹመቱ የጸደቀላቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችም ሀገርን እና ህዝቡን ለማገልገል ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በሚመለከት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡

የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን እና የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይም ተወያይቶ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

በየሻምበል ምሕረት

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.