Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ደህንነት መርህን እንዲጠብቅ አሳሰበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት የጋራ ደህንነት መርህን እንዲጠብቅ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የቻይና ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ ጄንግ ሹዋንግ ጠይቀዋል፡፡

ዲፕሎማቱ በትናንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እና በአውሮፓ ህብረት ትብብር ላይ የጋራ ደህንነትን ሀሳብ እንዲያፀድቅ የአውሮፓ ህብረትን ጠይቀዋል።

ቻይና በተመድ ቻርተር ዓላማዎች እና መርሆዎች መሰረት የተመድ እና የአውሮፓ ህብረት ትብብርን እንደምትደግፍም አመላክተዋል፡፡

ዲፕሎማቱ የአውሮፓ ህብረት የጋራ ደህንነት ሀሳቡን እንዲያጸድቅ የጠየቁት ለዓለም ሰላም እና ደህንነት የበለጠ አስተዋፅዖ እንዲያደርግ እና ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በማሰብ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ቻይና እንዲህ ዓይነቱ ትብብር በእውነተኛ የባለብዙ ወገን መርሆዎች፣ የጋራ ደህንነትና ለሰው ልጆች የጋራ መፃኢ ዕድል ሀላፊነቷን እንደምትወጣም ጠቅሰዋል።

የአውሮፓ ህብረት የባለብዙ ወገን ትብብር ተሟጋች እንደመሆኑ የተመድ ቻርተር ዓላማዎችን እና መርሆዎችን በማክበር እንዲሁም ዓለም አቀፍ ህጎችን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን መርሆዎች በማክበር እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡

የባለብዙ ወገን ትብብር ስርዓትን ከተመድ ጋር በመጠበቅ እና በባለብዙ ወገን ትብብር አርማ ስር ባሉ ሀገራት መካከል አብሮነትን እና እድገትን ለማጎልበት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የአንድን ሀገር ደህንነት በሌሎች ደህንነት ማስጠበቅ አይቻልም ያሉት ጄንግ፤ ወታደራዊ ቡድኖችን በማጠናከር እና በማስፋፋት ቀጣናዊ ፀጥታን ለማስፈን አይቻልም ሲሉ መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.