Fana: At a Speed of Life!

የመደመር ትውልድ መጽሐፍ በትረካ ለአድማጭና ተመልካች ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው የመደመር ትውልድ መጽሕፍ በትረካ፣ በዘጋቢ ፊልምና በሌሎች አማራጮች ለአድማጭና ተመልካቾች ሊቀርብ ነው።

አዲስ ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ትረካና ሌሎች ፓኬጆች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ሌንሳ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፣ የአዲስ ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ መሃመድ ሀሰን፣ አርቲስቶችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ከመርሐ ግብሩ ጎን ለጎን የመደመር ትውልድ ጽንሰ ሀሳብ፣ ሀገራዊ አበርክቶው፣ የትውልዱ ቀጣይ የቤት ሥራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ደዔታ ሌንሳ መኮንን የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ትውልድን መገንባት የሁሉም ዜጋ የቤት ስራ መሆኑን እንደሚያመላክት ጠቁመው÷ይህን ለማስረፅም መገናኛ ብዙሃን ሃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ በበኩላቸው÷የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።

አዲስ ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የመፅሐፉን ትረካ፣ ዘጋቢ ፊልምና ሌሎች ፓኬጆች ለአድማጭ ተመልካች ተደራሽ እንደሚያደርግ መገለጹንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.