Fana: At a Speed of Life!

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ባዕሉን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት በዓለ ትንሳኤ የእግዚአብሄር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል።

በዓለ ትንሳኤውን ስናከብርም ለእግዚአብሄር ክብርና ለሰው ልጆች ደኀንነት በአንድነት በመቆም መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የትንሣኤ በዓል የክርስቶስን መነሣት ያስተማረን የምሥራች መሆኑንም ተናግረዋል።

የትንሳኤ በዓል ሲከበር የችግሮች ሁሉ መውጫ ቁልፍ ሰላም ብቻ በመሆኑ በትንሳኤው ብርሃን ለሀገርና ለህዝብ የሰላም መሣሪያ በመሆንና ለሰላም በመፀለይ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ምዕመኑ የትንሳኤን በዓል ሲያከብር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።

በክርስቶስ ትንሳኤ ሁሉም በፍቅር ልብና በይቅርታ ለሰላምና አብሮነት በመጸለይ በዓሉን እንዲያከበርም መልክት አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.