Fana: At a Speed of Life!

በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ሞሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች ተቋረጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው እና በአብዲ ሞሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች ለህዝብ ጥቅም ሲባል እንዲቋረጡ መወሰኑን አስታወቀ።

በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ስር ያሉ ተከሳሾች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ወንጀል ክስ ክርክር ሲካሄድ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

በሌላ በኩል የእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የክስ መዝገብ በአንደኛ የህገ-መንግስትና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት የክርክር ሂደት ላይ መቆየቱ የሚታወቅ ነው።

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴርም ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም ሲባል እነዚህ የክስ ሂደቶች እንዲቋረጡ መወሰኑን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.