Fana: At a Speed of Life!

ምሽት ላይ በሚከናወኑ ሁለት የፍጻሜ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት ላይ በሚካሄዱ የ800 ሜትር እና የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው፡፡

በዚሁ መሠረት የሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ምሽት 4 ሠዓት ከ5 ደቂቃ ላይ የሚካሄድ ሲሆን÷ በዚሁ ዘርፍ አትሌት አስቴር አሬሬ እና ፅጌ ዱጉማ ይጠበቃሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ከ35 ደቂቃ ላይ በሚካሄደው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ኃ/ማርያም አማረ፣ ንብረት መላክ እና ገመቹ ዲዳ ተጠባቂ ናቸው፡፡

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው በጋና አክራ እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ዛሬ በርካታ የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች እንደሚካሔዱ የወጣው መርሐ-ግብር ያሳያል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.