Fana: At a Speed of Life!

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶች 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን በፅጌ ዱጉማ አማካኝነት አግኝታለች፡፡

ፅጌ ውድድሩን በ1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ74 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ነው የጨረሰችው፡፡

ፅጌ ባለፈው ወር በተደረገው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ማሸነፏ ይታወሳል።

ሌሎች በፍፃሜው የተሳተፉ አስቴር አሬሪ እና አዳኑ ኔንኮ በሜዳልያ ዝርዝር ውስጥ ሳይገቡ ቀርተዋል።

በሰለሞን በቀለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.