Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከግሪክ አቻቸው ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከግሪክ ፕሬዚዳንት ካትሪና ሳኬላሮፖሉ መኖሪያ ቤት ተገኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም፥ በኢትዮጵያና ግሪክ መካከል ያለውን ታሪካዊ የወዳጅነት እና የትብብር ትስስር በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ እና ግሪክ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀው፥ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የግሪክ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያውያን በግሪክ እንደሚኖሩ ሁሉ ለብዙ አስርት አመታት ተለዋዋጭ እንቅስቃሴ የነበረው የግሪክ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚኖር አንስተዋል፡፡

አክለውም፥ ዳያስፖራው በሀገራቱ መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እና ትብብርን የሚያጠናክር ድልድይ ሆኖ ባህልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአቴንስ እየተካሄደ ያለውን የሴቶች የፖለቲካ መሪዎች ጉባኤ ምክንያት በማድረግ በግሪክ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.