Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ አፍሪካ ሶስት ሀገራት የሚተገበር “ስካይ-በርድ” ሁለት የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ አፍሪካ ሶስት ሀገራት የሚተገበር “ስካይ-በርድ” ሁለት የተሰኘ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡

ፕሮጀክቱ በሴቶች እኩልነት እና አካታችነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚተገበር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ በዚሁ ወቅት÷”ስካይ-በርድ” ሁለት ፕሮጀክት ለአምስት ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል ብለዋል።

በሴቶች እኩልነትና አካታችነት ላይ ትኩረት በማድረግ በኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳና ዩጋንዳ ተግባራዊ የሚደረገው ፕሮግራም ከ200 ሺህ በላይ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 4 ሚሊየን ዩሮ እንደተመደበ በመግለጽ 80 በመቶው በኦስትሪያ ልማት ማህበር እና ቀሪው 20 በመቶው ደግሞ በኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማህበርና በስዊዘርላንድ የተፈጥሮ ልማት የሚሸፈን ይሆናል ብለዋል፡፡

በኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማህበር የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ተመስገን አበበ በበኩላቸው÷ተግባራዊ የተደረገው ስካይ-በርድ አንድ ከ210 ሺህ በላይ ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

የኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማህበር ስካይ-በርድ ሁለት ፕሮጀክት ግቡን እንዲመታ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት በሁሉም መስኮች ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የጠቆሙት ደግሞ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ሲሞን ክናፕ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.