Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች።

በርቀቱ ለኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ ያመጡት አትሌት ሂሩት መሸሻ እና አትሌት ሀዊ አበራ ናቸው።

በውድድሩ አትሌት ሂሩት መሸሻ 4:05.71 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤ ሀዊ አበራ ደግሞ 4:06.09 በሆነ ሰዓት በመግባት አትሌት ሂሩትን ተከትላውድድሩን በ2ኛነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አምጥታለች።

በውድድሩ የተሳተፈችው ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ቢቂሌ አንበሱ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በተመሳሳይም በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ሩጫ አትሌት ኤርሚያስ ግርማ ውድድሩን 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አምጥቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.