Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድርን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድርን በ18 ሜዳሊያ ናይጄሪያን በመከተል በ2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ላለፋት አምስት ቀናት በጋና አክራ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል።

 

በውድድሩ ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ በ87 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን 7 የወርቅ፣ 7 የብር እና 4 የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ችላለች፡፡

በውድድሩ ላይ ከ50 የአፍሪካ ሀገሮች ከ640 በላይ አትሌቶች መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.