Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል።

አለልኝ የእግርኳስ ህይወቱን በአርባምንጭ ከተማ ክለብ የጀመረ ሲሆን በባህርዳር ከተማ ለሁለት ዓመታት ምርጥ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን በማሻሻል ምርጥ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ለመሆን በቅቶ የነበረው አለልኝ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ አድርጎለት በዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ተሳትፎ ሲያደርግ ነበር።

ወጣቱ የአማካይ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከወራት በፊት ጋብቻ ፈጽሞ የትዳር ህይወት ይመራ ነበር።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተጫዋቹ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ እንዲሁም ለመላው የእግርኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.