Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ባለሙያ ሴቶች ኔትዎርክ በይፋ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ባለሙያ ሴቶች ኔትዎርክ (ኒውፊን) በይፋ ተመሰረተ።

የፋይናንስ ባለሙያ ሴቶች ኔትዎርክ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በዓለም ባንክ ትብብር የተመሰረተ ሲሆን የፋይናንስ ተጠቃሚነትን ከማሳደግ ባለፈ በዘርፉ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ሂደት ሴቶች የራሳቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር ያለመ ስለመሆኑም ተነስቷል።

በመርሐ ግብሩ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ÷ በፋይናንስ አካታችነት መርሐ-ግብር በወንዶችና ሴቶች መካከል ያለው የተሳትፎና የተጠቃሚነት ድርሻ ተመጣጣኝ አለመሆኑን አንስተዋል።

የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂው በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለውን ልዩነት የማጥበብ ዓላማን የሰነቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘላቂነትና መተማመን ያለበት የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት አካታች የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት የሚሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የሴቶች የፋይናንስ አካታችነትን ከግብ ለማድረስ የኔትዎርኩ መመሥረት ትልቅ አስቻይ አደረጃጀት እንደሆነ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

የኔትወርኩ ዓላማ ሴቶችን የሚያበቃና የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍን የፋይናንስ ዘርፍ ማጎልበት እንደሆነ ገልፀው፤ ለዚህ ጥረት የዓለም ባንክን ድጋፍ አድንቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.