Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የ4 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት እና በግል አጋርነት መርሐ-ግብር ከጊፍት ሪል ስቴት ጋር በመተባበር የ4 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ማስጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ያስጀመርናቸው 4 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ከ 14 እስከ 22 ወለል ያላቸው ዘመናዊ ሕንጻዎች ናቸው ብለዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮችን ከሕግና አሰራር ጋር በማጣጣም ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ምቹ የስራና የመኖሪያ ከተማ ለማድረግ መስራታችንን ቀጥለናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.