Fana: At a Speed of Life!

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ ሂደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል እየተገነባ የሚገኘውን የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ ፕሮጀክትን የሚያከናዉኑ ተቋራጮች ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የሚጠበቅባቸዉን ሀላፊነት እንዲወጡ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ ምክትል መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ሸበሌይ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘዉ የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ2ኛዉ ምዕራፍ በሀገሪቱ ከሚያስገነባቸው የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከላት መካከል አንዱ መሆኑ መገለጹን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን መረጃ አመልክቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.