ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
ተቋሙ በኢትዮጵያ የዲጂታል ሳምንት መርሀ ግብር ካለፉት ቀናት ጀምሮ ሲያካሂድ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የ2025 ዕቅድን እውን ለማድረግ ብሎም የፋይናንስ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የዲጂታል ሳምንቱ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር እንደሆነ ተመላክቷል።
መድረኩ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓቱ የዘመነ እንዲሆንና ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲኖር የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም አካታችነትና ዘላቂነት ያለው የፋይናስ ስርዓት ለመፍጠር በሚደረጉ ጥረቶች መድረኩ ግንዛቤ እንደሚፈጥር ተመላክቷል።
ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ ያዘጋጀው መድረክ የፋይናንስ ተቋማት የተደራሽነት አቅምን በማሳደግ ቀላል የክፍያ መንገዶች፣ አካታችና ግልፅ የሆነ የፋይናንስ ስርዓት በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።
በታሪኩ ወ/ሰንበት