Fana: At a Speed of Life!

አማኑኤል ገብረሚካኤል በጉዳት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የፋሲል ከነማው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ፡፡

በውድ የዝውውር ገንዘብ ፋሲል ከነማን የተቀላቀለው አማኑኤል÷ ክለቡ ትላንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አቻ በተለያየበት ጨዋታ ከግብ ጠባቂው ጋር በመጋጨቱ ነው ከባድ የእግር ጉዳት ያስተናገደው፡፡

የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጉዳቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷”ጥቃቅን የሚመስሉ ጉዳቶችና የጭካኔ ታክሎች ብዙ ተጫዋቾችን ከህልማቸው እያሰናከሉ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በግጭቱ  አማኑኤ ገብረ ሚካኤል ሁለት አጥንቱ መሰበሩን የገለጹት አሰልጣኙ ÷ በዚህም ላልተወሰነ ጊዜ ከእግር ኳስ መራቁ ግድ ሆኗል ብለዋል ፡፡

ስለሆነም በጨዋታ ላይ የሚስተዋሉ መሰል ጥፋቶችን ፕሪሚየር ሊጉ ሕግ ሊያበጅላቸው እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡

ተጫዋቹ በፍጥነት አገግሞ ወደ ክለቡ እንዲመለስም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ባጋጠመው ከባድ የቀርጭምጭሚት ጉዳት እስካሁን ያላገገመ ሲሆን÷ በዚህም ከብሄራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ ሆኖ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በተመሳሳይ የብሄራዊ ቡድን አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከባድ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ዋሊያዎቹ በቀጣይ በሚያደርጓቸው አህጉራዊ  ጨዋታዎች ላይ የአጥቂ ክፍተት እንዳይገጥማቸው ተሰግቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.