Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ተወዳዳሪዎች ነገ ለፍጻሜ ለማለፍ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው 4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜ ለማለፍ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡

በግማሽ ፍጻሜ ውድደርሩ ትዕግስት አስማረ፣ ሄኖክ ብርሃኑ፣ ባምላክ ቢያድግልኝ፣ ሀብታሙ ይሄነው እና በረከት ደመወዝ ይሳተፋሉ፡፡

በነገው ውድድር ከአምስቱ ተሳታፊዎቸ አንዱ ተወዳዳሪ የሚሰናበት ሲሆን÷ አራቱ ደግሞ ለፍጻሜው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ።

በዕለት አቀራረብ ላይ ብቻ መሰረት ያደረገው የፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር አቅም ኖሯቸው መድረክ ላጡ ባለተሰጥኦዎች መድረክ መስጠት እና የሙዚቃውን ዘርፍ ማበረታታት አላማው ነው።

በ4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አንደኛ ለሚወጣው (ለአሸናፊው) 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በአጠቃላይ ለውድድሩ ደግሞ የ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

ከአምስቱ ተወዳዳሪዎች እነማን ወደ ፍጻሜው ያልፋሉ የሚለውን ከዳኞች ጋር አድማጭ ተመልካቾችም አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ የሚወስኑ ይሆናል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አድማጭ ተመልካቹ የነገውን አጓጊ እና ጠንካራ ፉክክር በፋና ቴሌቪዥን፣በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ፣ በፋና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ጨምሮ በ www.fanabc.com ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት በመከታተልና በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናና እንዲደግፍ ጋብዟል፡፡

በለምለም ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.