Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፉ።

12፡00 ላይ በተካሄደው የድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለድሬዳዋ ከተማ በ73ኛው ደቂቃ ካርሎስ ዳምጠው፤ በ76ኛው ደቂቃ እስማኤል አብዱል ጋንዩ ሲያስቆጥሩ፤ ለፋሲል ከነማ በ13ኛው ደቂቃ ላይ ምኞት ደበበ ከሽንፈት ያላዳነውን ጎል አስቆጥሯል።

እንዲሁም 10፡00 ላይ በተደረገው ሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ቡና ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

መስፍን ታፈሰ በ4ኛው እና በ35ኛው ደቂቃ እንዲሁም ራምኬል ጀምስ በ90+7 ደቂቃ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ኢትዮጵያ ቡና አሸንፎ ወጥቷል።

እስራኤል እሸቱ በ83ኛ እና አብዱልባሲጥ ከማል በ90+4 ደቂቃ ላይ የሀዋሳ ከተማ ጎሎችን አስቆጥረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.