Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 2 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 2 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡

ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኬቨን ዴብሮይን (2)፣ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ሪኮ ሌዊስ ከመረብ ሲያሳርፉ÷ የክሪስታል ፓላስን ጎሎች ደግሞ ማቴታ እና ኤድዋርድስ አስቆጥረዋል።

ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎም ነጥቡን ወደ 70 በማሳደግ በሊቨርፑል በግብ ክፍያ ተበልጦ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ቤልጂየማዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ኬቨን ዴብሮይን ለማንቼስተር ሲቲ ያስቆጠራቸውን ግቦች 100 ማድረስ ችሏል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ-ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 1፡30 አርሰናል ከብራይተን ይጫወታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.