Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበርሊን፣ ማድሪድ እና ዴጉ ከተሞች በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

በበርሊን በተካሄደው የሴቶች የግማሽ ማራቶን ውደድር አትሌት ሙላቷ ተክሌ ርቀቱን 1 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በማጠናቀቅ ስታሸንፍ÷ በዚሁ ርቀት የተሳተፈችው አትሌት ፍታው ዘርዓይ 1 ሠዓት ከ7 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሆናለች፡፡

በሌላ በኩል በማድሪድ ከተማ የተካሄደውን የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት አበራሽ ከበደ 1 ሠዓት ከ8 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በደቡብ ኮሪያ ዴጉ በተደረገው የወንዶች ማራቶን ውድድርም አትሌት ጀማል ይመር ርቀቱን 2 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሲያሸንፍ÷ በዚሁ ቦታ እና ርቀት በሴቶች የተካሄደውን ውድድር አትሌት የብርጓል መለሰ 2 ሠዓት ከ19 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.