በሀርቡና ደጋን ከተሞች ሀገራዊ ለውጡን አስመልክቶ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡና ደጋን ከተሞች ሀገራዊ ለውጡን አስመልክቶ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ።
በድጋፍ ሰልፉ ለክልላችን ሰላም በህብረት እንቆማለን፣ ለሀገራችን ብልፅግና እውን መሆን እንተጋለን፣ በጋራ ጥረት ሰላማችንን እናረጋግጣለን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በተጨማሪም በጥቂት ፅንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገርና ህዝብ የለንም፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬችን መገለጫ ነው፣ የክልላችንን አንፃራዊ ሠላም በአጭር ጊዜ ወደ ዘላቂ ሠላም እናሸጋግረዋለን የሚሉ ድምጾችም በድጋፍ ሰልፉ መሰማታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡