Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት አርሰናል ከባየር ሙኒክ እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከማንቸስተር ሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ በድንቅ ብቃት ላይ የሚገኙት መድፈኞቹ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ባቫሪያኑን በኢምሬትስ የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም በሻምፒዮንስ ሊጉ እርስ በእርስ ባደረጓቸው 12 ጨዋታዎች ባየር ሙኒክ 7 ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ሲሆን÷አርሰናል በ3 ጨዋታዎቸ አሸንፏል፤በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የአምናው ሻምፒዮን ማንቸስተር ሲቲ ወደ ስፔን ተጉዞ በሳንቲያጎ በርናባው ሪያል ማድሪድን ይገጥማል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.