Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ፓሪሴንት ዥርሜን ከባርሴሎና እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦርሽያ ዶርትመንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ፒኤስ ጂ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በፓርክ ዴስ ፕሪንስ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ 4 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን÷ በሁለት ጨዋታዎች ፒ ኤስ ጂ ሲያሸንፍ÷ በተመሳሳይ በሁለቱ ደግሞ ባርሴሎና ማሸነፍ ችሏል፡፡

ባርሴሎና በፈረንጆቹ 2017 በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤነሪኬ እየተመራ ከሜዳው ውጭ በፒኤስ ጂ  የገጠመውን የ4 ለ 0 ሽንፈት በመቀልበስ  በካምፕኑ 6 ለ 1 አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያለፈበት ታሪካዊ ክስትተ አይዘነጋም፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ፔኤስ ጂ ዶናሩማ፣ ዛየር ኤምሬይ፣ ማርኪኒዮስ፣ ሉካስ ፈርናንዴዝ፣ ሜንዴዝ፣ ቪትንሃ፣ ኡጋርቴ፣ ሪዩዝ፣ ዴምቤሌ፣ ምባፔን እና ባርኮላን በቋሚ አሰላለፍ እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ባርሴሎና ቴር ስቴግንን፣ ኩንዴ ፣አሩዋዮ፣ ኩባርሲ፣ ዦአዎ ካንሴሎ፣ ዲ ጆንግ ክርስቲያንሰን፣ ጎንዶጋን፣ ላሜይን፣ ሌዋንዶውስኪ እና ራፊኒሃን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ እንደሚያካትት ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦርሽያ ዶርትመንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በስፔን ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሩብ ፍጻሜው 4 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን÷ ሁለቱን አትሌቲኮ ማድሪድ ሲያሸንፍ÷ ሁለቱን ደግሞ ቦርሽያ ዶርትመንድ አሸንፈፏል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንስ ሊጉ እርስ በርስ የተገናኙት በፈረንጆቹ ህዳር ወር 2018 ሲሆን÷ በጨዋታው አትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ጎል ዶት ኮም ባወጣው ግምታዊ አሰላለፍ በአትሌቲኮ ማድሪድ በኩል ጃን ኦብላክ፣ ዊሴል፣ ሂሜኔዝ፣ ሄርምሶ፣ ሎሬንቴ፣ ኮኬ፣ ዲ ፖል፣ ሳኦል፣ ሊኖ፣ ግሬዝማን እና አልቫሮ ሞራታ በምርጥ 11 አሰላለፍ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

በዶርትመንድ በኩል ደግሞ ኮቤል፣ ሪርሰን፣ ሀመልስ፣ ሾልተርቤክ፣ ማቲሰን፣ ኢምሪ ቻን፣ ሳቢዘር፣ ጃደን ሳንቾ፣ ብራኒት፣ አዲየሚ እና ፋልከርግ በምርጥ 11 ውስጥ ይካተታሉ፡፡

ትናንት በተካሄዱ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች አርሰናል ከባየርን ሙኒክ 2 አቻ እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ 3 አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.