Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ ዓረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ሥራ ነገ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን በተቀናጀ መንገድ የመመለሱ ሥራ ነገ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ።

በሚኒስትር ዴኤታዋ የተመራው የመንግሥት ልዑክ ቡድን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲና የጂዳ ቆንስላ ጀነራል ሰራተኞች እና የኮሙኒቲ አስተባባሪዎች ጋር ተወያይቷል።

በዚህም በተመላሾች መለየትና መመለስ ላይ የስራ አቅጣጫ መሰጠቱም ነው የተጠቆመው።

ሚኒስትር ዴኤታዋ በዚህ ወቅት ፥ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራው ዜጋ ተኮር የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊነትን ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

አክለውም ፥ ሪያድ እና ጂዳ አካባቢ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት የመመለሱ ስራ ነገ እንደሚጀመር አቅጣጫ ተቀምጦ ዝግጅቱ ተጠናቋል ነው ያሉት።

የልዑካን ቡድኑ ከጅዳ አስተዳደሮች ጋር ውይይት በማድረግ በሽመሲ ማቆያ ጣብያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መጎብኘቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.