Fana: At a Speed of Life!

የዓባይ ተፋሰስ “ቤዚን ፕላን” አተገባበር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓባይ ተፋሰስ “ቤዚን ፕላን” አተገባበር የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት ከክልሎች የፕላንና ልማት ቢሮዎች ጋር ተደርጓል።

የፊርማ ሥነ-ስርዓቱ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የውሃና ኢነርጂ ቢሮዎች፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት ነው የተደረገው፡፡

ስምምነቱ የውሃና ኢነርጂሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) እና ክልሎችን በመወከል የፕላንና የልማት ቢሮ ሃላፊ ተወካዮች መካከል መፈረሙም ተነግሯል፡፡

ስምምነቱ የተዘጋጀው የዓባይ ቤዚን ፕላን ወደ መሬት ወርዶ እንደየዘርፎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

የቤዚን ፕላኑ አተገባበር አደረጃትና የአመራር ሂደትን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይትም መካሄዱን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የዓባይ ቤዚን ፕላኑ የተቀዱ የውሃ ምደባ እቅድ፣ የውሃ ጥራት ስራዎች እቅድ፣ የተፋሰስ ልማት እቅድ፣ የተፋሰስ መረጃ አስተዳደር እቅድ፣ የዌትላንድ ማኔጅመንት እቅድ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸውም ነው የተገለጸው፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.