Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ።

ዛሬ ምሽት 1፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ በ30ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ባህር ከተማ ሲመራ ቢቆይም፤ በጭማሪ ሰዓት 90+5′ ላይ አማኑኤል ኤርቦ ባስቆጠራት ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ቀን 10፡00 ላይ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የሀምበሪቾ ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.