Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ከጀርመን ኩባንያ ጋር የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከጀርመን ድርጅት አስተባባሪ ቢሮ (አይ ኤፍ ኢ) ጋር የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል።

የኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ÷ የጀርመኑ ማስተባበሪያ ቢሮ የስራ እድልን ለመጨመር እና የአምራች ኩባንያዎችን አቅም ለማሳደግ ለያዘው እቅድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አድንቀዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑም ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ በሙሉ አቅም እንዲተገበር በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀስ አረጋግጠዋል።

ድጋፉ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ፣ የአምራች ኩባንያዎችን እርካታ በመጨመር ፓርኩ በሙሉ አቅሙ እንዲንቀሳቀስና ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ እና የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብና እድገት ሚኒስትር ማስተባበሪያ ዶሚኒካ ፕሪይዚንግን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ሃላፊዎች መገኘታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.