Fana: At a Speed of Life!

የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል እድሳት ስራ 75 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል እድሳት ስራ 75 በመቶ መድረሱን የካቴደራሉ አስተዳደርና ሰበካ ጉባኤ አስታውቋል፡፡

የእድሳት ስራውን ለማጠናቀቅ 85 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግና 172 ሚሊየን ብር ውል ተፈፅሞ እድሳቱ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተነግሯል።

የካቴደራሉ አስተዳደርና ሰበካ ጉባኤ እድሳቱ ያለበት ሁኔታና ቀሪ ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት እድሳቱ የተጀመረው ካቴደራሉ 75 ከመቶ መጠናቀቁን እና ለእድሳቱ እስካሁን 90 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉም ተገልጿል።

የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል የእድሳት ስራን ከሦስት ወር በሗላ ሙሉ ለሙሉ ለመጨረስ እቅድ መኖሩ የተጠቆመ ሲሆን ፥ እድሳቱ እንዲጠናቀቅ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደረግ ተጠይቋል።

በቀጣይ ለእድሳቱ ማጠናቀቂያ የሚፈለገውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የገንዘብ ማሰባሰብ መርሐ ግብር እንዲሁም ሚያዝያ 19፣ 2016 ዓ/ም የቀጥታ ስርጭት የገንዘብ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ይካሄዳል ተብሏል።

በተጨማሪም ገንዘቡን ለማሰባሰብ ባንኮችና ሌሎች አማራጮች መቅረባቸው ተገልጿል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.