Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድና ኮቬንትሪ ሲቲ ዛሬ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛና በጭማሪ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡

በዚህም ዩናይትድ በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ለዋንጫው መፋለም የሚያስችለውን ድል አስመዝግቧል፡፡

ቀያይ ሰይጣኖቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎም ቀደም ሲል ቼልሲን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፋቸውን ካረጋገጡት ውኃሰማያውዮቹ ጋር የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

ባለፈው ዓመት ሁለቱም የማንቼስተር ከተማ ክለቦች ለፍፃሜ ደርሠው ማንቼስተር ሲቲ የከተማ ተቀናቃኙን 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን መውሰዱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.