Fana: At a Speed of Life!

አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደግፍ  የተሻለ የስራ እድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደግፍ  የተሻለ የስራ እድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

“ኢትዮጵያ-ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ሃሰብ የተዘጋጀው የኢንዱስትሪዎች ምርታማነት የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩን አስመልክተው ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ በተዘጋጀ የንቅናቄ ማጠቃለያ መድረክ ላይ በመገኘት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ተወያይተን ወደ ላቀ ደረጃ የተሸጋገሩ አምራቾችን ሸልመናል ብለዋል።

የሚሰሩ እጆችን ከስራ እያገናኘን፣ የሚፈጥር አዕምሮን ወደ ተግባር እያስገባን ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያነሷቸውን ቅሬታዎች በመፍታት የተሻለ የስራ እድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል።

አስተዳደሩ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለውን የድጋፍ ማዕቀፍ በፍትሃዊነት በማስተናገድ እና ጉድለቶችን በጋራ በመሙላት ለወጣቶች በቂ የስራ እድል የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመገንባት እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.