Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት ለትውልድ ህዝባዊ ንቅናቄ ከ25 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ከ25 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሃብት መሰብሰቡን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ንቅናቄው ግለቱን ጠብቆ ሊቀጥል እንደሚገባ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል።

ትምህርት የሁሉም መሠረት እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትር ዴዔታዋ÷ በትምህርት ሥርዓቱ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን መሠረት ለመጣል ጠንክሮ መሥራት ይገባል ብለዋል።

በዚህም የትምህርት ስብራቱን ለማከም የሚያስችል አሻራ መጣልና ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት፡፡

አሁን ላይ በትምህርት ዘርፉ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተጀመሩ ሥራዎችን የበለጠ ለማሳደግ በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት አመራሮቹ እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

በንቅናቄው በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከ25 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሃብት ማሰባሰብ መቻሉንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በትምህርት ዘርፉ የተካሄደው የትምህርት ለትውልድ የት/ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ ህብረተሰቡ በትምህርት ላይ ያለውን የባለቤትነት ሚና በትክክል ያረጋገጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.